ኢትዮጵያዊ ባምላክ ተሰማ የ2018ቱን የዓለም ዋንጫ እንዲዳኙ ተመረጡ

ህዳር 22፣2010

ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር ባምላክ ተሰማ በመጪው ክረምት በሩሲያ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ እንዲመሩ ከተመረጡት ዳኞች መካከል አንዱ ሆኑ፡፡

ፊፋ 36 ዳኞችን ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ይፋ አድርጓል፡፡ አውሮፓ 10 ዳኞችን በማስመረጥ ቀዳሚ አህጉር ሆኗል፡፡ አፍሪካ ደግሞ 6 ዳኞችን አስመርጣለች፡፡

ባምላክ ተሰማም አፍሪካን ወክለው የዓለም ዋንጫን ከሚመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሆነዋል፡፡ ይህም ለኢትዮጵያ ዳኞች መልካም ስም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ባምላክ ተሰማ ጥሩ ዳኝነት ማሳየታቸው አይዘነጋም፡፡

ባምላክ ተሰማ  ለኢትዮጵያ ዳኞች ግልጋሎት የሚውል ቁሳቁስ በራሳቸው ወጪ በማበርከት የአገሪቱን እግር ኳስ ዳኞች ብቃት ለማሻሻል የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሆነ በኢትዮጵያ ዳኞች ኮሚቴ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡

ምንጭ፡‑ ደች ሪፈሪ እና ቫንጋርድ ናይጀሪያ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች