የ2018 የቻን አዘጋች ሃገር በመጪው ቅዳሜ ይፋ ይደረጋል

ጥቅምት 2፤2010

የአፍሪካ እግር ካስ ፌዴሬሽን ካፍ የ2018 ቻን አዘጋጅ ሀገር በመጪው ቅዳሜ ይፋ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡

ኬንያ የ2018ቱን ቻን ለማዘጋጀት እድል የተሰጣት ቢሆንም በበቂ ሁኔታ ውድድሩን ለማዘጋጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ ኢትዮጵያ፤ ሞሮኮ እና ኢኳቶሪያ ጊኒ ውድድሩን ለማዘጋጀት ለካፍ ጥያቄ ያቀረቡ ሃገራት ሆነዋል፡፡

በሀገር ውስጥ ሊጎች ብቻ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚደረገው የቻን ውድድር በየአመቱ ጥር ወር የሚካሄድ ሲሆን የ2018 አዘጋጅ ሀገርን ለመምረጥ የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ ይወሰናል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ኮሜት ረቡዕ እለት ባደረገው ስብሰባ ላይ የካፍ ፕሬዠዳንት አህመድ አህመድ ካሜሮን የ2019ን አፍሪካ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ  
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች