የ2017 የባላንዶር ዕጬ ተሸላሚዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ

መስከረም 30፤2010

ባላንዶር ወይም ፍሬንች ጎልደን ቦል በየአመቱ ጥሩ ብቃት ያሳዩ እግር ኳስ ተጫዎቾች የሚመረጡበት  ሽልማት ሲሆን በፈረንጆቹ 2017 ሰላሳ ተጫዎቾችን ይፋ አድርጓል፡፡

ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ የ2017 ባላንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይሆናሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡ 

ከተመረጡት 30 ተጫዎቾች ውስጥ የአውሮፓ ቻምዮንስ ሊግ እና የላሊጋው አሸናፊ ሪያል ማድሪድ 7 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ  ሲሆን ካሪም ቤንዜማ፣ኢስኮ፣ራሞስ፣ማርሴሎ፣ ቶኒ ክሮስ እና ሉካስ ሞድሪች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ባርሴሎና በበኩሉ በሉዊስ ሱዋሬዝና በሊዮኔል ሚሲ ሲወከል  አትሌቲኮ ማድሪድ በአንቶን ግሪዝማን እና በግብ ጠባቂው ጃን ኦብላክ ተወክሏል፡፡

ከእንግሊዝ ክለቦች መካከል ደግሞ ቼልሲ ኢንጎሎ ካንቴንና እና ኤደን ሃዛርድን ሲያስመርጥ  ሊቨርፑል ሴኢዶ ማኔና እና ኮቲንሆን በማሰመረጥ ቀዳሚ ሆነዋል፡፡

ቶተንሃም በበኩሉ ሃሪ ኬንን፤ ማንችስተር ዩናይትድ ድቪድ ዲሂሃን እና  ማንችስተር ሲቲ ዴብሮንን አስመርጠዋል፡፡

የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂውን ቡፎን እና ፓውሎ ዲባላን በዝርዝሩ ውስጥ ማካተት ችሏል፡፡ 

ሌሎች ዕጬዎች ሮበርት ሎዋንዶስኪ፣ ማት ሃምለስ ከባየር ሙኒክ ፤ ኔይማር ፣ምባፔ ከፒ ኤስ ጂ፤  ኤዲን ዚኪ ከሮማ ፤ኤምሪክ ኦባሚያንግ ከዶርቱመንድ፣ ራዳሜል ፋልካዎ ከሞናኮ፣ ሊዎናርዶ ቦችኒ ከኢሲ ሚላንና፣ዲሪስ ሞርተን ከናፖሊ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ ተጫዎቾች ናቸው፡፡

ምንጭ፡ ጎል ዶትኮም

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች