በ2018ቱ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኮትዲቯር፤ ዛምቢያና ዩጋንዳ ድል ቀንቷቸዋል

ነሃሴ 28፤2009

ለ2018ቱ የሩሲያ አለም ዋንጫ ማጣሪያ በተደረጉ ጨዋታዎች ዛምቢያ አሌጄሪያን 3ለ1 በሆነ ያለተጠበቀ ውጤት አሸንፋለች፡፡

ሃያላኑ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ናይጄሪያና ካሜሮን ተገናኝተው ናይጄሪያ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች፡፡

በሌሎች ጨዋታዎችም ኬፕ ቨርዴ ደቡብ አፍሪካን 2ለ1፤ ሞሮኮ ማሊን 6ለ0፤ ቱኒዚያ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 2ለ1፤ ኮትዲቯር ጋቦንን 3ለ0፤ ዩጋንዳ ግብጽን 1ለ0፤ ጊኒ ሊቢያን 3ለ2 አሸንፈዋል፡፡

የየምድቡን ሰንጠረዥ ስንመለከት

 ምድብ አንድን ቱኒዚያ በዘጠኝ ነጥብ ስትመራ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ በስድስት ነጥብ ትከተላለች፡፡

ምድብ ሁለትን ናይጄሪያ በዘጠኝ ነጥብ ስትመራ ዛምቢያ በአራት ነጥብ፤ ካሜሮን በሁለት ነጥብ እንዲሁም አልጄሪያ በአንድ ነጥብ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ምድብ ሶስት ላይ ደግሞ ኮትዲቯር በሰባት ነጥብ መሪ ስትሆን ሞሮኮ በአምስት ነጥብ ትከተላለች፡፡

ቡርኪና ፋሶ በአምስት ነጥብ ምድብ አራትን የምትመራ ሲሆን ሰኔጋል እና ደቡብ አፍሪካ በእኩል አራት ነጥብ እንዲሁም ኬፕቬርዴ በሶስት ነጥብ ተከታትለው ይገኛሉ፡፡

ምስራቅ አፍሪካዊቷ ዩጋንዳ ደግሞ በሰባት ነጥብ ምድብ አምስትን ስትመራ ግብጽ በስድስት፤ ጋና በሁለት ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

በአፍሪካ አህጉር ገናና ታሪክ ያላቸው እንደ ጋና፤ ካሜሮን አልጄሪያ ያሉ ሀገራት ከአሁኑ የውጤት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ ዩጋንዳና ቡርኪና ፋሶ ታሪካቸውን ለማደስ የተቃረቡ ሀገራት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ፤ ሱፐር ስፖርት

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች