አርሰናል በሜዳው ማንችስተር ዩናይንድ አስተናግዶ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል

ሚያዝያ 30 ፣ 2009

ትላንት በተደረገው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል በሜዳው ማንችስተር ዩናይንድ አስተናግዶ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በ25 የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጎዞው  ትላንት በአርሰናል ተገቶበቷል፡፡

ብዙ ሙከራዎች ያለታየበት  የመጀመሪያው  አጋማሽ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡በሁለተኛው አጋማሽ ዣካ በ54ኛው  ደቂቃ አርሰናል ቀዳሚ የሚያደርገውን  ጎል ሲያስቆጥር ከሶስት ደቂቃቆች በኃላ የቀድሞው  የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዎች ዳኒ ዌልቤክ በግንባሩ  ሁለተኛውን የአርሰና ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

ከግቧ መቆጠር በኃላ ራሽፎርድ እና  ሊንጋድን ወደ ሜዳ ቀይረው  ያስገቡት አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኖ የጨዋታውን ውጤት መቀየር ሳይችሉ ጨዋታው በአርሰናል 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ትላንት በተካሄደው ሌላኛው   የፕሪሚየር ሊጉ  ጨዋታ ሊቨርፑልና ሳውዝ ሀምፕተንን ያፋጠጠ  ነበር፡፡ በዚሁ ጨዋታ  ሁለቱም  ቡድኖች ያለውጤት ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል፡፡

አርሰናል የትላንቱን ድል ተከትሎ  ከማንችስተር ዩናይትድ በ2 ነጥብ ዝቅ ብሎ  በ6ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ማንችስተር ሲቲ በ4ኛ  ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ቸልሲ ፣ቶተንሃምና ሊቨርፑል የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች በቅደም ተከተል እንደያዙ ነው፡፡  

ሊጉ ዛሬም  ሲቀጥል መሪው ቼልሲ በሜዳው ሚድልስቦሮን ያስተናግዳል፡፡

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች