ማንችስተር ዩናይትድና ሮስቶቭ በዩሮፓ ሊጉ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተለያዩ

መጋቢት 01 ፣ 2009

 

የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተደርገዋል።

ከሜዳው ውጪ ከሩሲያው ሮስቶቭ ጋር የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ በ35ኛው ደቂቃ በሄንሪክ ሚኪታሪያ ጎል መምራት ሲችል፣ ባለሜዳዎቹ በ53ኛው ደቂቃ በቡካሮቭ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ጥሩ እንቅስቃሴ ባልታየበት የሁለቱ ጨዋታው ዩናይትዶች የተሻለ እድል ይዘው ጨዋታውን አጠናቀዋል፡፡

በሌላ የምሽቱ ጨዋታ በሜዳው አያክስ አምስተርዳም ያስተናገደው ኮፐንሃገን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የጀርመኖቹ ሻልካ እና ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በምሽቱ ከፍተኛ ትኩረትን ያገኘው የፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ሊዮን እና የጣሊያኑን ሮማ ጨዋታ ባለሜዳው ሊዮን ጨዋታውን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡

በዚህም  ለመልሱ ጨዋታ የማለፍ እድሉን አስፍቷል፡፡

 አፖል ኒኮሲያ አንደርሌክትን አስተናግዶ 1 ለ 0 ሲሸነፍ፥ የስፔኑ ሴልታቪጎ የሩሲያውን ክራስኖዳር 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

 የኦሎምፒያኮስ ከቤሺክታሽ ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል፡፡

የጥሎ ማለፉ የመልስ ጨዋታዎች መጋቢት 7 የሚደረጉ ሲሆን ሩብ ፍጻሜውን የሚቀላቀሉ ቡድኖች የሚለዩ ይሆናል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች