በካልካታ 25 ኪሜ ሩጫ ላይ ቀነኒሳ በቀለ ይሳተፋል

ህዳር 02፤2010

በመጪው ሳምንት በህንድ ካልካታ በሚካሄደው የ25 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ ቀነኒሳ በቀለ የሚያደርገው ፉክክር ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱም ሆነ በሃገሪቱ ይህን ውድድር ሲያደርግ የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የርቀቱ ክብረወሰን የተያዘው በኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ ሲሆን ሰዓቱም 1:11:18 ነው፡፡ ቀነኒሳም ይህንን ሰዓት ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቀነኒሳ በሰጠው አስተያየትም በህንድ ውድድር ለማድረግ ብዙ ጠብቅያለሁ፤ ይህን እድል በመጠቀምም አዲስ ታሪክ ለመስራት እፈልጋለሁ ብሏል፡፡

በሴቶቹ ደግሞ ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት ከወዲሁ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷታል፡፡

ምንጭ፡ አለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች