ኢትዮጵያ በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ 24 ደረጃዎችን አሽቆለቆለች

መስከረም 05፤2010

ፊፋ ባወጣው የወሩ  የአለም ሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ  ኢትዮጵያ ከነበረችበት 120ኛ ደረጃ  ወደ 144ኛ ስታሽቆለቁል ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ 44ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ግብፅ ከአፍሪካ ሀገራት አንደኛ ስትሆን ከዓለም ደግሞ አምስት ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 30ኛ ደረጃ ላይ  ተቀምጣለች፡፡

ቱኒዚያ ሶስት ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 31ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ግብፅን ተከትላ 2ኛ ሆናለች። ሴኔጋል ደግሞ ሁለት ደረጃዎችን በመቀነስ ከዓለም 33ኛ ከአፍሪካ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በአለም አቀፍ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃን ደግሞ ጀርመን ብራዚልን በማስከተል አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ፖርቹጋል ከባለፈው ወር ሶስት ደረጃዎችን በማሻሻል ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች።

አርጀንቲና ፥ቤልጂየም፥ፖላንድ፥ስዊዘርላንደ ፈረንሳይ፥ቺሊ እና ኮሎምቢያ ደግሞ ከአንድ እስከ አስር ያለውን ደረጃ መቆናጠጥ ችለዋል፡፡

ኬፕ ቨርዲ 47፣ ሉክሰምበርግ 35 መቄዶኒያ 32 እንዲሁም ቆጵሮስ 24 ደረጃዎችን በማሻሻል የተሻለ ወርሃዊ ደረጃ ያስመዘገቡ ሀገራት ሲሆኑ  ጓቲማላ 31 እና ኢትዮጵያ 24 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል የከፋ ውጤት አስመዝግበዋል።

ምንጭ፡ ፊፋ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች