በ16ኛው የለንደን አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ለተሳተፉ አትሌቶች ሽልማት ተሰጠ

መስከረም 3፣2010

መንግስት በ16ኛው የለንደን አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ለተሳተፉ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት ልዑካን ቡድን የእውቅና ሽልማት ሰጠ፡፡

ትናንት መስከረም 2፣2010 ዓ.ም በሀዋሳ በተካሄደው የእውቅናና የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ በሻምፕዮናው የወርቅ ሜዳልያ ላስገኙ አትሌቶች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱን የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሻምፕዮናው የአገራቸውን መልካም ገጽታ ከፍ ለማድረግ አትሌቶች በግላቸው የከፈሉት መስዋእትነት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች