ከ18 አመት በታች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ወርቅ አገኘች

ሐምሌ 06፤2009

በኬኒያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው ከ18 አመት በታች 10ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

ከባድ ፉክክር በታየበት ውድድሩን አበራሽ ምንስዎ በ9 ደቂቃ ከ24 ነጥብ 62 ሰከንድ በሀገሯ እና በደጋፊዋ ፊት የሮጠችውን ኬንያዊቷን በመቅደም አንደኛ  ሆናለች፡፡

 ኬንያዊቷ ኢማኩሌቴ ቼፕክሩይ በ9 ደቂቃ ከ24 ነጥብ 69 ሰከንድ ሁለተኛ ስትሆን ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊቷ ይታይሽ መኮንን ደግሞ በ9 ደቂቃ ከ28 ነጥብ 46 ሰከንድ ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች። 

ዛሬም ሲቀጥል በሴቶች 400 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ አትሌት ሀና አምሳሉ እና በወንዶች 400 ሜትር መልካሙ አሰፋ የግማሽ ፍጻሜ ውድርራቸውን  ይደረጋል።

የደረጃ ሰንጠረዥን ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በአንድ የወርቅ እና አንድ የብር ሜዳልያ ስትመራ ኢትዮጵያ በአንድ ወርቅ ነአንድ ነሃስ ሁለተኛ ጀርመን በአንድ ወርቅ ሶስተኛ ያለው ደረጃ ይዘዋል፡፡

ምንጭ፡ አለም አቀፉ አትሌቲክስ ፈደሬሽን
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች