በ28ኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ

ግንቦት 09፣2009

በ28ኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አበባ ከተማን አስተናግዶ 2ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡

በጨዋታው በ38ኛው ደቂቃ አቡበከር ነስሩ የመጀመሪያ እና ሳሙኤል ሳኑሚ በ44ኛው ደቂቃ ሁለተኛው ጎል ማስቆጠር ችለዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና 47 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ  ሲዳማ ቡና በእኩል 47 ነጥን በግብ ክፍያ ተበልጦ 4 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አዲስ አበባ ከተማም ከአንድ ዓመት የፕሪምየር ሊግ ቆይታ በኋላ ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዱ ተረጋግጧል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ነገም ቀጥሎ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ፋሲል ከተማ ከመከላከያ፣ ወልድያ ከጅማ አባ ቡና፣ ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከደደቢት እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ያደርጋሉ።

ፕሪምየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ52 ነጥብ ሲመራ፤ ደደቢት በ48፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና በእኩል 47 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች