ሃይለ አምላክ የ10ሺህ ሜትር ወንዶች አሸናፊ ሆነ

ግንቦት 08፣2009

በ46ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 10ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ የሲዳማው ሃይለአምላክ ሳይጠበቅ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በውድድሩ 80 አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሃይለአምላክ ውድድሩን በበላይነት ለማጠናቀቅ 28፡32 ደቂቃ ወስዶበታል፡፡ ሙክታር እንድሪስ እና አባዲ አዲስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡

አባዲ አዲስ የባለፈው ዓመት ሻምፒዮን በመሆኑ በዛሬው ውድድርም ከፍተኛውን ግምት አግኝቶ ነበር፡፡

ሙክታር እንድሪስ ውድድሩን በበላይነት እንዳጠናቀቀ በማሰብ መጨረሻ ላይ መዘናጋቱ ድሉ ወደ ሃይለአምላክ እንዲያመራ አድርጓል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በዕለቱ ሶስተኛ ወርቁን አግኝቷል፡፡ መከላከያ እና እና ኦሮሚያ ደግሞ አንድ አንድ ወርቅ ወስደዋል፡፡

ውድድሩ ነገም የሚቀጥል ሲሆን የ4 መቶ፣ የ8 መቶ እና 1 መቶ ሜትር ውድድር ፍፃሜዎች ይጠበቃሉ፡፡

በአዝመራው ሞሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች