ዋልያዎቹ በሴካፋ በብሩንዲ አቻቸው ተሸነፉ

ህዳር 28፣2010

በኬንያ እየተካሄደ ባለው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 ተሸንፏል።

                      ፎቶ ፡ ከፋይል

ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ለኢትዮጵያ ዳዋ ሁቴሳ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ በዚህም ሁለቱም ቡድኖች ለእረፍት 1አቻ በሆነ ውጤት ወጥተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከእረፍት መልስ ብሩንዲዎች አከታትለው ባስቆጠሯቸው ሶስት ግቦች አሸንፈው ወጥተዋል፡፡

በዚህም ዋልያዎቹ በቡሩንዲ አቻቸው 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማክሰኞ ደቡብ ሱዳንን ገጥሞ 3 ለ 0 ማሸነፍ ቢችልም ሁለተኛ ድሉን በብሩዲ አቻው ላይ መድገም ሳይችል ቀርቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች