ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ- ኤሌክትሪክ ሶስት ነጥብ ወሰደ

ህዳር 25፣2010

በ5ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ጨዋታውን ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3ለ1 አሸነፈ፡፡

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ምንተስኖት አዳነ በመጀመሪያው ግማሽ፣ አብዱል ከሪም እና አዳነ ግርማ በሁለተኛው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በካሉሻ አማካኝነት ከባዶ መሸነፍ ያዳነችውን ግብ አግኝቷል፡፡

ከሶስት ጨዋታዎች 7 ነጥብ መያዝ የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ ይጠብቀዋል፡፡

አዳማ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ጅማ አባጅፋር በበኩሉ ጨዋታውን ያለ ምንም ግብ አጠናቋል፡፡ ጀማ አባጅፋር ከ5 ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻለው 4 ነጥብ ብቻ ነው፡፡ተጋጣሚው ሲዳማ ቡናም በተመሳሳይ ጨዋታዎች 4 ነጥብ ይዟል፡፡

ደደቢት ከፋሲል ከነማ 11፡30 በአዲስ አበባ ስታዲዮም ያደረጉት  ጨዋታም ካለ ምንም ግብ 0ለ0  ተጠናቋል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች