በጣሊያን ሴሪ አ ቤኔቬንቶ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብ ጠባቂው አንድ ነጥብ አገኘ

ህዳር 24፤2010

በጣሊያን ሴሪ አ 15ኛ ሳምንት በተደረገው ጨዋታ ቤኔቬንቶ ከኤሲ ሚላን ጋር ሁለት አቻ በመውጣት ግብ ጠባቂው ብሪግኖሊ በ95ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ በሴሪ አ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

ቤኔቬንቶ ካደረጋቸው 14 ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ ወይ አቻ መውጣት ያልቻለ ሲሆን በአንድ ነጥብ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በአውሮፓ ካሉት አምስት ትላልቅ የሊግ ክለቦች ውስጥ 14 ጨዋታዎችን በተከታታይ በመሸነፍም ቤኔቬንቶ ክብረ ወሰን ይዟል፡፡

ብሪግኖሊ ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ በሰጠው አስተያየት "በቃ አይኔን ጨፍኜ ዘለልኩ በጭንቅላቴም አስቆጠርኩ ምክንያቱም የፊት መስመር ተጫዋች አይደለሁም" ብሏል፡፡

ከፈረንጆቹ 2001 ወዲህ በሴሪ አ ግብ በማስቆጠር ብሪግኖሊ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ሆኗል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች