አዳማ ከተማና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቱ ድል ሲቀናቸው ኢትዮጵያ ቡና ተሸንፏል

ህዳር 24፤2010

በአምስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 በማሸነፍ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ መምራት ችሏል፡፡

ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ከድር ሳሊህ በ81ኛው ደቂቃ ነበር፡፡

በዚሁ ውጤትም አዲግራት ወልዋሎ ዩኒቨርሲቲ ሊጉን በዘጠኝ ነጥቦች እየመራ ይገኛል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከተማ ሃዋሳ ከተማን 1ለ0፤ አርባምንጭ ከተማ መከላከያን 2ለ0 አሸንፈዋል፡፡

ለአዳማ ከተማ ኤፍሬም ዘካሪያስ በ18ኛው ደቂቃ እንዲሁም ብርሃኑ አዳሙና ጸጋዬ አበራ ደግሞ ለአርባምንጭ ከተማ ሁለቱን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ወላይታ ዲቻና ድሬደዋ ከተማ ደግሞ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ወልዋሎ አዲግራት በዘጠኝ ነጥብ ሲመራ አዳማ ከተማ በስምንት ነጥብ 2ተኛ፤ ኢትዮጵያ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያለው በሰባት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች