የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉም ጨዋታዎች እሁድ እና ሰኞ ይካሄዳሉ

ህዳር 22፤2010

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉም ጨዋታዎች እሁድ እና ሰኞ በክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ፡፡

እሁድ በክልል ከተሞች 5 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን፣ ወልድያ ከተማ መቐለ ከተማን፣ አርባ ምንጭ ከተማ መከላከያን፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ኢትዮጵያ ቡናን እንዲሁም ወላይታድቻ ድሬዳዋ ከተማን በሜዳቸው በተመሳሳይ ከቀኑ 9 ሰዓት ያስተናግዳሉ፡፡

ሰኞ ደግሞ ጅማ አባጅፋር አዳማ ላይ ሲዳማ ቡናን እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በተመሳሳይ 9 ሰዓት ይገጥማሉ፡፡

ጅማ አባጅፋር በሜዳው የሚያደርግውን ጨዋታ ወደ አዳማ ያዞረው በቅጣት ምክንያት ነው፡፡

ሰኞ ምሽት 11፡30 ደደቢት ፋሲል ከተማን የሚገጥምበት የአዲስ አበባ ስታዲዮም ጨዋታ የሳምንቱ መርሃ ግብር ማሳረጊያ ይሆናል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች