ኢትዮጵያ ቡና መሪነቱን አጠናክሯል

ህዳር 18፤2010

ዛሬ በተካሄደው አራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አርባምንጭ ከተማን 2ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና በረከት ሽመልስ በ32ኛ እና የአርባምንጭ ተጫዋች አሌክስ አማዙ በ71ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቀጠረው ግብ ሙሉ ሶስት ነጥቦችን ይዞ መውጣት ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ቀሪ አንድ ጨዋታ እያለው በሰባት ነጥብ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል፡፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ ሃዋሳ ከነማ፤ ደደቢት እና መቀሌ ከተማ እያንዳንዳቸው አራት ጨዋታዎችን ተጫውተው በተመሳሳይ ስድስት ጨዋታዎች ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

በነገው እለት ደግሞ ሲዳማ ቡና የአምናውን ሻምፕዮን ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት በአንድ ነጥብ ብቻ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና በበኩሉ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በሶስት ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች