ሰለሞን ባረጋ እና ዘይነባ ይመር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነዋል

አዳዲስ አሸናፊዎች በተስተዋሉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሰለሞን ባረጋ እና ዘይነባ ይመር አሻናፊ ሆነዋል፡፡

ለ17ኛ ጊዜ በተካሄደው የ10 ኪ.ሜ ኢንተርናሽናል ውድድር በወንዶች ሰለሞን ባረጋ ማሸነፍ ችሏል፡፡

አዲስ አሸናፊዎች በተሰተዋሉበት የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በወንዶች ዘርፍ ሞገስ ጥዑማይና ዳዊት ፍቃዱ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ምድብ ደግሞ ዘይነባ ይመር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሻናፊ መሆን የቻለች ሲሆን ግርማዊት ገ/እግዛብሄር እና ፎተን ተስፋዬ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ለየምድቡ አሸናፊዎች 100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

44 ሺህ ተሳታፊዎች በሆኑበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአሸናፊዎች በጠቅለላ 300 ሺህ ብር መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በዘንድሮው ውድድር 500 የውጭ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሲ ኤን ኤን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሚድያዎች ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ሽፋን ሰጥተዋል፡፡

ከውድድሩ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለዕርዳታ እንደሚዉል የታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች