ኬንያዊቷ የሪዮ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና አትሌት በታላቁ ሩጫ ትሳተፋለች

ህዳር 15፣2010

ኬንያዊቷ የሪዮ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና ቪቪየን ችሩዮት በፊታች እሁድ በሚካሄደው ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ እንደምትሳተፍ ተገለጸ፡፡

የአውሮፓውያኑ 2016 የሪዮ ኦሎምፒክ የ5 ሺህ ሜትር አሸናፊ አትሌቷ በውድድሩ ላይ የምትሳተፈው በክብር እንግድነት ተጋብዛ ነው ተብሏል፡፡

የታለቁ የኢትዮጵያ ሩጫ ዳይሬክተር አቶ ኤርሚያስ አየለ የኦሎምፒክ ሻምፒዮናዋ አትሌት በውድድሩ ላይ መሳተፍ ሩጫውን አለም አቀፋዊ ለማድረግ ከታሰቡ ሰፊ ስራዊች አካል ነው ብለዋል፡፡ 

ታላቁ ሩጫ ጤናማ የህይወት አኗኗርንና ስፖርታዊ ሩጫን እንደሚያበረታታም ተናግረዋል፡፡

10 ሺህ ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው ውድድር ላይ 47 ሺህ 500 ሯጮች ተሳታፊ ይሆኑበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በውድድሩም ላይ 2 ሺህ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎችና ቱሪስቶች ይታደማሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አይንስሊቭ ድረ-ገጽ

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች