የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊና ስራ አስፈጻሚ ምርጫው እንዲራዘም ወሰነ

ጥቅምት 30 ፤2010

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያካሄደ ባለው 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የፕሬዝዳንታዊና የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር ወስኗል፡፡

ከዚህ ውሳኔ በፊት ከአማራ፤ ኦሮሚያና አፋር ክልሎች የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ተወካዮች የምርጫው ጊዜ እንዲራዘም ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

በቀረበው ጥያቄ ላይ የፌዴሬሽኑ አባላት ውይይት ካደረጉ በኋላ በአብላጫ ድምጽ ምርጫው እንዲራዘም ወስነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ምርጫው እንዳይራዘምና በተቀመጠለት ጊዜ እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህን ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ከፊፋ ፍቃድ እንዳገኘ ገልጿል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች