• የኬንያዊቷ የኦሎምፒክ ማራቶን አሸናፊ ለአራት አመት ታገደች

ጥቅምት 29፣2010

ኬንያዊቷ የሪዮ የኦሎምፒክ ማራቶን አሸናፊ ጂማ ሰምጎንግ አበረታች መድሃኒት ተጠቅማለች በሚል ለአራት አመት  ከውድድር ማገዱን የኬንያ የጸረ አበረታች ኤጀንሲ ገለጸ፡

አትሌቷ  ባደረገችው ምርመራ በደሟ ውስጥ የአበረታች መድሃኒት ከተገኘባት በኋላ ውሳኔ ማስተላለፉን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

ጂማ ሰምጎንግ ባለፈው ዓመት  በሪዮ ኦሎንፒክ  የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት በኦሎንፒክ ማራቶን ያሸነፈች  የመጀመሪያዋ የኬንያ አትሌት ናት፡፡

አትሌቷ በሚያዘያ ወር ያደረገችው ምርመራ አልተሳካም ነበር፡፡ የአራት አመት አገዳው ከባለፈው ሚያዘያ ወር ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጉዳዩ የኬንያ ጸረ አበረታች ኤጀንሲ ለስፖርት ክርክሮች ፍርድ ቤት በመውሰድ በአለም ጸረ አበረታች ኤጀንሲ የሚመከር አንደሚሆን ተገልጿል፡፡

 

 አትሌቷ  ስህተት መፈጸሟን  አሳዛኝ አጋጣሚ መሆኑን ጉዳዩ የያዘው የአለም አቀፉ ጸረ አበረታች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የ32 ዓመቷ ጂማ ሰምጎንግ እንደተናገረችው በኬንያ ሆስፒታል በእርግዝና ምክንያት ምርመራው እንዳልተሳካ ብትናገረም የስፖርት ክርክሮች ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል፡፡

ሰምጎንግ  የቀድሞው የቦስተን እና የቺካጎ ማራቶን ሻምፒዮን ከሆነው ከሪታ ጄፕቶ በኋላ በጸረ አበረታች ምርመራ የወደቀች የመጀመሪያ የኬንያ አትሌት ሆናለች፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች