ዴቪድ ሞዬስ አዲሱ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

ጥቅምት 28 ፤2010

ዌስትሃም ዩናይትድ የክለቡን ዋና አሰልጣኝ ስላቫን ቢሊችን በማሰናበት የቀድሞውን የኤቨርተንና የማንቸቨስተር ዩናይትድ አሰላጣኝ የነበሩትን ዴቪድ ሞዬስን መሾሙን ገልጿል።

ዴቪድ ሞዬስም  በዌስትሃም የሁለት ዓመት ተኩል ስምምነት ሲያደርጉ ክለቡን አሁን ከገባበት የወራጅ ቀጣና የማውጣት ስራ ይጠብቃቸዋል፡፡

ልምምዳቸውን ዛሬ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

በባለፈው ሳምንቱ ዌስትሃም በሊቨርፑል የ4 ለ 1 ሽንፈትን በኃላ አሰልጣኝ ስላቫን ቢሊችን ለማሰናበት ተገዷል ሲሉ የክለቡ ሊቀመንበር ዲቪድ ሱሊቫን ተናግረዋል፡፡  

ስላቫን ቢሊችን በዌስትሃም ክለብ ለሁለት አመት ከ6 ወራት ቆይታ አድርገዋል።

ክለቡ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች በ2 ብቻ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በ2 አቻ በ7ቱ ተሸንፎ 9 ነጥብ በመሰብሰብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ምንጭ ፡ ዘ ሰን

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች