አልማዝ አያና የዓመቱ ምርጥ አትሌት ለመባል ከመጨረሻዎቹ 3 ዕጩዎች ተካተተች

ጥቅምት 27፤2010

አትሌት አልማዝ አያና የዓመቱ ምርጥ አትሌት ለመባል ከመጨረሻዎቹ ሶስት ዕጩዎች ተካተተች፡፡

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የዓመቱም ምርጥ አትሌት ለመምረጥ በሁለቱም ፆታዎች 6 አትሌቶችን የመጨረሻ ዕጩ አድርጎ አቅርቧል፡፡

የባለፈው ዓመት አሸናፊዋ አልማዝ አያና በዚህ ዓመትም ትጠበቃለች፡፡

በሴቶች አልማዝ አያና ከግሪኳ  አትሌት ኤካትሪኒ ስቴፋኒዲ  እና ከቤልጀሟ  አትሌት ኒፋሳቶ ቲሃም  ጋር ተፋጣለች፡፡

ኤካትሪኒ በምርኩዝ ዝላይ የኦሎምፒክ ወርቅ እና የተለያዩ ሻምፒዮናዎችን ያነሳች አትሌት ነች፡፡ 

በተለያዩ ወድድሮች የምትታወቀው ኒፋሳቶ ቲሃም  ደግሞ በተለይ  በከፍታ እና በሌሎች የዝላይ ዓይነቶች ስም የያዘች አትሌት ነች፡፡

በወንዶች ደግሞ ሙታዝ ኢሳ ከኳታር፣ ሞፋራህ ከእንግሊዝ እንዲሁም ዋይድ ቫን ከደቡብ አፍሪካ ለውድድር ቀርበዋል፡፡

የፌደሬሽኑ  ምክር ቤት እና  ከፌደሬሽኑ ጋር የሚሰሩ አካላት  የሚሰጡት ድምፅ ከደጋፊዎች የቀጥታ የኦላይን ድምፅ ጋር ተደምሮ የመጨረሻ አሸናፊዎች ይለያሉ፡፡

አሸናፊው ከ18 ቀን በኋላ ይታወቃል፡፡ አልማዝ አያና ድል የሚቀናት ከሆነ ኢትዮጵያ በሴቶች ለተከታታይ ሶስት ዓመታት ድሉን ማንሳት ትችላለች፡፡ እ.አ.አ በ2015 ገንዘቤ ዲባባ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች