በሳምንቱ ጨዋታ የለንደንና የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ፉክክር ተጠባቂ ሆኗል

ጥቅምት 24፣ 2010

በ11ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እሁድ የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በሜዳው ከማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም  ማንቸስተር ሲቲ ከአርሴናል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ቼልሲ በሳምንቱ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በሮማ ከደረሰበት የ3ለ0 ሽንፈት ለማንሰራራት እንደሚጫወት አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ተናግረዋል፡፡

ቼልሲ በፕሪምየር ሊጉ ካደረጋቸው አስር ጨዋታዎች በ3ቱ ሲሸነፍ በ19 ነጥቦች አራተኛ ደረጃን በመያዝ ነው ከዩናይትድ ጋር ጨዋታውን የሚያደርገው ፡፡

ዩናይትድ ሰባት ጨዋታዎችን በማሸነፍ በ23 ነጥብ 2 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የአንቶኒዮ ኮንቴው ቼልሲ በባለፈው ዓመት በሜዳው ዩናይትድን 4 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በሌላ ጨዋታ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው የፕሪምየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሰቲ በሜዳው ኢታድ 5ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን አርሰናልን ያስተናግዳል፡፡

ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች ውስጥ ዘጠኙን ሲያሸንፍ በአንዱ ብቻ አቻ በመውጣት በ28 ነጥብ ፕሪምየር ሊጉን ይመራል፡፡

በአንጻሩ አርሰናል በ19 ነጥብ 5 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ 

ሌሎች ጨዋታዎች ስቶክ ሲቲ ከሌስተር ሲቲ፤ ኒውካስል ዩናይትድ ከቦርንመዝ፤ ስዋንሲ ሲቲ ከብራይተን ከውዝሃምፕተን ከበርንሌይ ሃደርስፊልድ ታውን ከዌስትብሮሚች አልቢዮን፤ ዌስትሃም ዩናይትድ ከሊቨርፑል፤ እሁድ ቶተንሃም ሆትስፐር ከክሪስታል ፓላስ ኤቨርተን ከዋትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (1 Vote)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች