አርሰናል በዩሮፓ ሊጉ ቀጣዩን ዙር ሲቀላቀል፣ ለኤቨርተን አልተሳካም

ጥቅምት 24፣2010

በዩሮፓ ሊግ አርሰናል ከሬድ ስታር በርግሬድ ጋር አቻ በመለያየት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን ውጤት አግኝቷል፡፡ በተቃራኒው ኤቨርተን በሊዮን 3ለ0 ተሸንፎ ከውድድሩ ወጥቷል፡፡

አርሰናል ጨዋታውን ያለግብ እንዲያጠናቅቅ የዥሩድ ተደጋጋሚ ግብ መሳት  ምክንያት እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

ጨዋታውን ተከትሎ አርሰናል ከ4 ጨዋታዎች በሰበሰበው 10 ነጥብ ወደ 32 አላፊ ቡድኖች መቀላቀሉን አረጋግጧል፡፡

ከሜዳው ውጭ በሊዮን 3ለ0 የተረታው ኤቨርተን የምድቡን ግርጌ ይዞ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል፡፡ ውጤቱ እንደሚያሳየው አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማንን የተኩት አሰልጣኝ አንስ ዎርዝ ያደረጉአቸውን ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል፡፡

የኤቨርተኑ ሸንደርሊን በ80ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

የምሽቱ አነጋጋሪ ጉዳይ የነበረው የቀድሞው የማንችስትር ዩናይትድ የአሁኑ የማርሴ ተጨዋች ፓትሪክ ኤቭራ ተቀይሮ ለመግባት እያሟሟቀ በነበረበት ወቅት ደጋፊውን በመማታቱ ወደ ሜዳ ሳይግባ በቀይ ካርድ ወጥቷል፡፡

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርም ጉዳዩን እየመረመረው ነው ተብሏል፡፡ በጨዋታው ማርሴ በጊዩማርስ 1ለ0 ተረቷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች