ኢትዮጵያዊው አትሌት የማራቶን ውድድሩን በነጠላ ጫማ አሸነፈ

ጥቅምት 22፤2010

ኢትዮጵያዊው አትሌት በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር በፕላስቲክ ነጠላ ጫማ በመሮጥ አሸናፊ ሆኗል፡፡

‹‹ሶንግሻን ሾሊን›› በሚባል አለም አቀፍ ማራቶን በሸበጥ ወይም ነጠላ ጫማ ተወዳድሮ አሸናፊ በመሆን በቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ የሆነው አትሌት አሞኘ ሰንደቁ አለልኝ ይባላል፡፡

አትሌቱ ውድድሩን ለመጨረስ 2 ሰዓት፣ ከ28 ደቂቃ፣ ከ2 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡

አትሌት አሞኘ ውድድሩን በነጠላ ጫማ ሲሮጥ አይተው የተደመሙ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎች የአትሌቱን ምስል ተቀባብለውታል፡፡

የአትሌቱን ብቃት ያሞካሹ አድናቂዎቹም ይህ የአትሌቱ ስኬት ማንኛውም አትሌት ውጪያዊ ድጋፍ ሳያስፈልገው ውድድሮችን ማሸነፍ እንደሚችል ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሀል ግን አትሌቱ በነጠላ ጫማ ማሸነፍ መቻሉን የተጠራጠሩ አንዳድ አድናቂዎች ደግሞ አትሌቱ ጫማው ላይ ባለ ምትሀታዊ ሀይል ለድል እንደበቃ ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ይሁንና በጉዳዩ ላይ አትሌቱ በአድናቂዎቹ ለተነሱለት ጥያቄ ሲመልስ ‹‹ውድድሩን ያሸነፍኩት በነጠላ ጫማው ላይ ባለ ልዩ ሀይል ሳይሆን ባጋጠመኝ መልካም እድል ነው›› ብሏል፡፡

አትሌት አሞኘ ሰንደቁ አለልኝ የማራቶን ውድድር አሸናፊ በመሆኑ የ20 ሺህ ዩዋን ተሸላሚ መሆን እንደቻለ ተገልጿል፡፡

አትሌት አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ የማይሻር ታሪክ መስራቱ ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ አትሌት አሞኘ ሰንደቁ አለልኝ በሸበጥ ሮጦ ባለድል መሆኑ ባለታሪክ አያስብለውም?

ምንጭ፦ ፒፕልስ ደይሊ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች