ፌደሬሽኑ ያቀረበው ጥያቄ በካፍ ውድቅ ሆነ

ጥቅምት 22፤2010

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር የቻን ማጣርያ ጨዋታውን ለማድረግ ለካፍ ያቀረበው የቀን ለውጥ ጥያቄ ውድቅ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በመሆኑም ፌደሬሽኑ ባለው ጊዜ ውስጥ ለመዘጋጀት እየሞከረ መሆኑን ገልጿል፡፡

ለቻን ተሳትፎ የሚያደርጉት የብሔራዊ ቡድኑ አባላትም ጥሪ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ጨዋታ እሁድ ጥቅምት 26 ቀን በአዲስ አበባ ስታድየም የሚደረግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ በሳምንቱ ኪጋሊ ላይ ይደረጋል።

ነገር ግን ካፍ እስካሁን ዳኞችን እንዳልመደበ በፌደሬሽኑ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ዜና ለፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ለመሆን የቀርቡ ዕጩዎች ቁጥር 5 መሆናቸውን ፌደሬሽኑ ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና ደቡብ ተወካዮቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ጋምቤላም በቅርቡ ዕጩ ማቅረቡ ታውቋል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች