በሻምፒዮንስ ሊጉ ቸልሲ ሲሸነፍ፣ ዩናይትድ ድል ቀንቶታል

ጥቅምት 22፣2010

በምሽቱ ከምድብ አንድ እስከ አራት የሚገኙ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች አራተኛ ዙር የመርሃ ግብር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

                         የቸልሲና ሮማ ተጨዋቾች የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ

ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልትራፎርድ ቤኔፊካን 2ለ0 ሲያሸንፍ፣ ቸልሲ ሮም ላይ በሮማ የ3ለ0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ በጨዋታው የቸልሲ ተከላካይ ክፍል ስህተቶችን በተደጋጋሚ ሲሰራ አምሽቷል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ ከ4 ጨዋታዎች ሙሉ 12 ነጥብ ማግኘት ቢችልም ከምድቡ ማለፊያ ነጥብ ገና አላገኘም፡፡ ለዩናይትድ ግቦችን የቤኔፊካው ግብ ጠባቂ እና ብሌንድ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ከዚሁ ምድብ ባዜል እና ሲኤስ ኬ ሞስኮ ተገናኝተው ሞስኮዎች 2ለ1 አሸንፈዋል፡፡
ፓርሴን ጀርመን አንደርሌክትን 5ለ0 የረታበት ጨዋታ የምሽቱ ብዙ ግብ የተስተናገደበት ጨዋታ ነው፡፡

በመሆኑም ፒኤስ ጂ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ ከዚሁ ምድብ ባየር ሙኒክ ሴልቲክን 2ለ1 አሸንፏል፡፡ በሌላ ጨዋታ ኦሎምፒያኮስ ከባርሲሎና ያለምንም ግብ ሲለያዩ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከጁቬንቱስ አንድ አቻ ወጥተዋል፡፡ አትሌቲኮ ማድሪድም ከአዘርባጃኑ ክለብ ኳልባግ  ጋር አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡

ሻምፒዮንስ ሊጉ ዛሬም ከምድብ 5 እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖችን ያገናኛል፡፡ ሪያል ማድሪድ እና ቶተንሃም ዊምብሌ ላይ የሚገናኙበት ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረትን ስቧል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ጨዋታቸው አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

ሊቨርፑል ከማሪቦር፣ ናፖሊ ከማንችስተር ሲቲ በዛሬው መርሃ ግብር የሚገናኙም ይሆናል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች