ብሄራዊ ቡድኑ ያለበቂ ዝግጅት በቻን እንደማይሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገለፀ

ጥቅምት 21፣2010

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ለቻን የአፍሪካ የአፍሪካ ለማለፍ ያለበቂ ዝግጅት ከሩዋንዳ አቻውን ጋር መጫወት እንደማይፈልግ ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ዕድሉ ስለተገኘ ብቻ  ሞራል የሚነካ ውጤት ባለበት ሁኔታ ያለበቂ ዝግጅት ጨዋታውን ማድረግ ተገቢ ሆኖ እንዳልተገኘ በፌደሬሽኑ  ተገልጿል፡፡

በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ኢትዮጵያ ሩዋንዳን ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ እንድታስተናግድ የወጣ ሲሆን ፣ የመልስ ጨዋታዋን ደግሞ  ህዳር 3  ኪጋሊ ላይ እንደምታደርግ ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የጨዋታው ቀን እንዲራዘም ካፍን መጠየቁ ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ካፍ የምድብ ድልድሉን ከ16 ቀናት በኋላ የሚያድርግ በመሆኑ የይራዘምልን ጥያቄውን ይቀበላል ተብሎ እንደማይጠበቅ የብዙዎች ግምት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ከውድድሩ መውጣት እርግጥ መሆን ግን ለሩዋንዳ መልካም ዕድል ይመስላል፡፡

በሌላ በኩል ብሄራዊ ቡድኑ ለቻን ለማለፍ ከሩዋንዳ ጋር  ያለመጫወት እድሉ እውን የሚሆን ከሆነ በዚህ ሳምንት እንደሚጀመር መርሃ ግብር የወጣለት እና የሊግ መቆራረጥ የማያጣው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሳይጀመር ከመቋረጥ የሚድን ይሆናል፡፡

ግብፅ የሊግ ውድድሯን ላለሟቋረጥ እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድኗ የዓለም ዋንጫ መዘጋጃ ሰፋ ያለ ግዜ ለመስጠት በማሰብ ከቻን እራሷን ማግለሏን ተክተሎ እድሉ ለኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ሆኗል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች