ከአስራ ሰባት አመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ያደርጋል

ጥቅምት 14 ፤2010

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአስራ ሰባት አመት በታች የ2018 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ ከናይጄሪያ አቻው ጋር እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ከኬንያ ጋር ተመድቦ የነበረው ብሄራዊ ቡድኑ የኬንያ ቡድን ለጨዋታው መዘጋጀት በለመቻሉ ጨዋታው ሳይደረግ መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ከአስራ ሰባት አመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያው ዙር ጨዋታውን ህዳር 22 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ጨዋታ ያደርጋል፡፡

ለ6ተኛ ጊዜ የሚካሄደው ከአስራ ሰባት አመት በታች የፊፋ የ2018 የዓለም ዋንጫ 16 ሀገራትን በማሳተፍ በደቡብ አሜሪካዋ ኡራጋይ በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት ህዳር ወር ላይ ይጀምራል፡፡

ምንጭ፤ ጎል ዶት ኮም

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች