ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ዋንጫን ለ5ኛ ጊዜ አነሳ

ጥቅምት 12፣2010

ቅዱስ ጊዮርጊስ 12ኛ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ዋንጫን ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለባዶ በመርታት በድል አጠናቋል፡፡

ጊዮርጊስ በመጀመሪያው አጋማሽ በ44ኛው ደቂቃ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የተቀላቀለው ኢብራሂማ ፎፋና ባስቆጠራት ግብ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት አጠናቋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ሲያነሳ ለ5ኛ ጊዜ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ምንም ግብ ሳያስቆጥር ከሜዳ ወጥቷል፡፡ ኢትዮያ ቡና ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ሁለት ጊዜ ያነሳ ሲሆን ፣የዛሬውን ጨዋታ በድል አጠናቆ ቢሆን ለሶስተኛ ጊዜ ድሉን ያጠጥም ነበር፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታው አሸናፊ በመሆኑ ዋንጫውን ከክብር እንግዶች እጅ  ተቀብሏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ካርሎስ ማንዌል ቫዝ ፒንቶ የውድድሩ ኮኮብ አሰልጣኝና ኒኬማ ዞኮ ኮኮብ ተጨዋች ተብለው ተሸልመዋል፡፡

 

የሁለቱ ክለቦች የሸገር ደርቢ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ጨዋታ ነበር፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስና ቡና እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች መካከል አላስፈላጊ ጥል ተፈጥሮ በጨዋው ላይ አሉታዊ ድባብ አሳድሮም ነበር፡፡

ከሁለቱ ክለቦች የዋንጫ ጨዋታ ቀደም ብሎ በጅማ አባ ጅፋርና በኢትዮ አሌክትሪክ መካከል በተካሄደ የደረጃ ጨዋታ፣ ጅማ አባ ጅፋር አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት አሸንፎ በሶስተኛነት አጠናቋል፡፡

ተሸናፊው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ አራተኛ ደረጃ በመያዝ የዘንድሮው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

ሪፖርተር፡‑ አዝመራው ሙሴ  

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች