ኬንያዊቷ አትሌት በሷ ተይዞ የነበረውን የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ዳግም አሻሻለች

ጥቅምት 12፣2010

የኬንያዊቷ አትሌት ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ በሷ ተይዞ የነበረውን የአለም ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ዳግም አሻሽላለች፡፡

አትሌቷ ዛሬ  በስፔን ቫሌንሲያ በተካሄደ ውድድረ  ግማሽ ማራቶኑን ለመጨረስ 1፡4፡52 ፈጅቶባታል፡፡ ባለፈው ሚያዚያ በፕራግ ሮጣ ክብረ ወሰን የሰበረችበትን ጊዜ በአሁኑ ሩጫዋ በአንድ ሰኮንድ አሻሽላ ገብታለች፡፡

ጄፕኮስጌ በዚህ ዓመት  ክብረ ወሰን በመስበር ውጤት ስታስመዘግብ የዛሬው ለ6ኛ ግዜ ነው፡፡

"በቫሌንሲያ ስሮጥ የመጀመሪዬ ነው፣ተደስቸበታለሁ፡፡አየሩ መልካም ስለነበር በፍጥነት ሮጬ እንዲጨርስ አስችሎኛል" ብላለች፡፡

ለባህሬን የሮጠው አብርሃም ቼሮበን በ59፡11 በሆነ ጊዜ በመግባት ቫሌንሺያ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ድሉን አጣጥሟል፡፡

ምንጭ፡‑ ሮይተርስ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች