ባርሲሎና፣ዩናይትድ እና ፒኤስ ጂ በሻምፒዮንስ ሊጉ ተከታታይ ድላቸውን አስመዝግበዋል

ጥቅምት 9፤2010

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የየምድቡ ሶስትኛ ዙር መርሃ ግብር ጨዋታዎች ትላንት ምሽት የተደረጉ ሲሆን ባርሲሎና፣ ማንችስትር ዩናይትድ እና ፒኤስ ጂ የሊጉን ሶስተኛ ድላቸውን አግኝተዋል፡፡

ጁቬንቱስ እና ባየር ሙኒክም በምሽቱ ባለድል ሲሆኑ ቸልሲ ከሮማ 3 አቻ ተለያይቷል፡፡

ማንችስትር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ባደረገው ጨዋታ በራሽፎርድ ብቸኛ ግብ ባለድል ሆኗል፡፡ ለግቧ መቆጠር በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የምንግዜውም ታዳጊው ግብ ጠባቂ የሆነው የቤኔፊካው ሚል ሲቪላር ጥፋት ነበረበት፡፡ ሲቪላር የያዛትን ኳስ ወደ ግብ ክልሉ ይዞ በመግባቱ ወደ ግብነት ተቀይራለችና፡፡

ሜሲ በአውሮፓ መድረክ 100ኛ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ  ባርሲሎና ኦሎምፒያኮስን 3ለ1 ረቷል፡፡ ዲያን እና ኒኮሉዋን ቀሪዎቹን የባርሲሎና ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ፓርሴን ጀርመን በማምፔ፣ ካፋኒ፣ ኔማር እና ዲማሪያ 4 ግቦች አንደርሌክትን 4ለ0 ረቷል፡፡ ፒኤስ ጂ በዓመቱ ጠንካራ ሆኖ መቅረቡን የሚያሳይ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡

በሜዳው ሮማን ያስተናገደው ቸልሲ በበኩሉ በሊዊዝ እና በሃዛርድ ግቦች 2ለ0 ከመምራት ተነስቶ 3 አቻ ተለያይቷል፡፡ ለሮማ ዜኮ ሁለት ግቦችን እንዲሁም ኮላሮብ ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ለቸልሲ ሃዛርድ 2 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡

ጁቬንቱስ ስፖርቲንግ 2ለ1፣ ባየር ሙኒክ ሴልቲክን 3ለ0 እንዲሁም ባዜል ሲኤስ ኮ ሞስኮን 2ለ0 አሸንፈዋል፡፡

ዛሬ ምሽት የኢሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች