ሊቨርፑል በሜዳው ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል

ጥቅምት 03፣2010

በ8ተኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምር ሊግ የሳምቱ ታላቅ ጨዋታ ሊቨርፑል በሜዳው  ማንችስተር ዩናይትድ ያስተናግዳል።

ዩናይትድ በዚህ የውድድር አመት ከተጀመረ ጠንካራ የሆነ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ዩናይትድ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዝ በከተማ ተቀናቃኙ በግብ ክፍያ ተበልጦ በ19 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሊቨርፑል በአንጻሩ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዩናይትድ በፕሪምር ሊጉ ካደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች 21 ጎሎች በማስቆጥር  በስድስቱ አሸንፎ በአንዱ አቻ ወጥቷል።

ሊቨርፑል ካደረጋቸው ሰባ ጨዋታዎች በሶስቱ ድል ሲቀናው አንድ አቻ ወጥቶ በ12 ነጥብ  ሰባተኛ  ደረጃ ላይ ይገኛል።

በነገው ጨዋታ ሊቨርፑል ስዶ ማኔን ባጋጠመው የሆድ ቁርጠት ምክንያት የማይሰለፍ ይሆናል። ማኔ ለስድስት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል

ፊሊፕን ኮንቲንኖ እና ሮቤርቶ ፌሚኖ ከብራዚል ተነስተው ረጅም ጉዞ ቢያደርጉም በጨዋታ ሊገኙ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

በዩናይትድ በኩል በሞሪኖ እምነት የተጣለበት ማሩዋን ፌላኒ ሀገሩ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት በጨዋታው ላይ የማይሰለፍ ሲሆን አንበሉ ማይክል ካሪክም የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል።

ተከላካዩ ፊል ጆንስ ከጉዳቱ አገግሞ በጨዋታ ሊሰለፍ ይችላል ተብሏል።

ሌሎች ነገ የሚደረጉ ጨዋታዎች በርንሌ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ክሪስታል ፓላስ  ከቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲ ከስቶክ ሲቲ፣ ስዋንሲ ሲቲ ከሃድርስፊልድ ታውን፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከቦርንመውዝ፣ ዋትፈርድ ከአርሰናል  ሲጫወቱ  እሁድ  ብራይተን እና ሆቭ አልቢዮን ከኤቨርተን ሳውዝሃምፕተን ከኒውካስል ዩናይትድ ሰኞ ሌስተር ሲቲ ከዌስትብሮሚች አልቢዮን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች