ፓናማ የአለም እግር ኳስ ማጣሪያ ማለፏን ተከትሎ ብሔራዊ በዓል አወጀች

ጥቅምት 1፤2010

ፓናማ በ2018 የሚካሄደውን የአለም እግር ኳስ የማጣሪያ ውድድርን ማለፏን ተከትሎ በውድድሩ መካፈሏን ካረጋገጠችበት ቀን በሃላ የሚገኘውን ዕለት ብሔራዊ በዓል እንዲሆን ማወጇን ገለፀች፡፡

በመካከለኛው አሜሪካ የምትገኘው ፓናማ እ.ኤ.አ በ2018 በሩሲያ በሚካሄደው የአለም የእግር ኳስ ውድድር ላይ መሳተፏን ያረጋገጠችው ኮስታሪካን 2 ለ1 በማሸነፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ትላንት የማጣሪያ ውድድሩ ማለፉን ካረጋገጠ በሃላ የፓናማ ፕሬዝዳንት ጆዋን ካርሎስ ቫሬላ በየዓመቱ ውድድሩን ያሸነፉበትን ማግስት የሀገሪቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተነግሯል፡፡

በዚህም ዕለት የግልም ሆነ የመንግስት ሰራተኞች ከመደበኛ ስራቸው የሚያርፉ ሲሆን ትምህርት ቤቶችም እንደሚዘጉ ተገልጿል፡፡

ፓናማ በአለም የእግር ኳስ ውድድር ስትሳተፍ በታሪክ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች