ናይጄሪያ ለዓለም ዋንጫ በማለፍ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች

መስከረም 28፣2010

ትናንት በተደረገው ጨዋታ ናይጄሪያ በሜዳዋ ዛምቢያ አስተናግዳ በአሌክስ ኢዮቢ ብቸኛ ጎል ወደ የ2018 የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ናይጄሪያ ምድብ 2 በ13 ነጥብ በአንደኝነት አጠናቃለች፡፡

በዚው ምድብ የምትገኘ ካሜሮን አልጄሪያን 2 ለ 0 ብታሸንፍም ወደ ሩሲያው የዓለም ዋንጫ መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች፡፡ ሌላዋ ተጠባቂ ሀገር አልጄሪያ ካደረገችው 5 የማጣሪያ ጨዋታዎች አንዱን ቻ አቻ ስትወጣ ሌሎቹን በመሸነፍ  የምድቡ ግርጌ ላይ በመቀመጥ አጠናቃለች፡፡

በምድብ አንድ መሪዋ ቱኒዝያ ከሜዳዋ ውጪ  ከጊኒ ያደረገችውን ጨዋታ  4 ለ 1 ማሸነፍ ችላለች፡፡

ለቱኒዝያ የሱፍ ማሳንኪ ሃትሪክ ሲሰራ ቀሪዋን ጎል  ማሃመድ ቤን አሞር ባለሜዳዎቹ ከሽንፈት ያላዳነች ጎል ኬታ አስቆጥሯል፡፡ቱኒዝያ በ13 ነጥብ ስትመራ  ወደ ዓለም ዋንጫው ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ ያስፈልጋታል፡፡

በዚው ምድብ ዲሞክራቲክ ጎንጎ ሊቢያን 2 ለ0 አሸንፋለች፡፡ ዲሞክራቲክ ጎንጎ ወደ ሩሲያ ለማቅናት በቀጣዩ በሚደረገው ጨዋታ ሊቢያ ቱኒዝያ ማሸነፍ ከቻለች ጊኒን በሰፊ ጎል ካሸነፈች ማለፏን ታረጋግጣለች፡፡

በመጨረሻ የምድቡ ጨዋታ ከወዲሁ አጓጊ መሆን ችሏል፡፡ኮትዲቯር ለማለፍ ብቸኛዋ አማራጭ ማሸነፍ ብቻ ነው፡፡

በምድብ 4  በሶስተኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ሴኔጋል ኬቬርሲን በማሸነፍ በ8 ነጥብ የምድብ አንደኛ መሆን ችላለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ቡርኪና ፋሶን  3 ለ 1 በማሸነፍ የቡርኪና ፋሶ የማለፍ ተስፋ አጨልማለች፡፡

በምድብ አምስት የተደረገው የጋና እና የዩጋንዳ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ዩጋንዳ መሪ የምትሆንበት ውጤት አበላሽታለች፡፡

ዛሬ በዚው ምድብ ግብፅ እና ኮንጎ ጨዋታቸው ያደርጋሉ፡፡ ግብጽ ጨዋታው ካሸነፈች ወደ ሩሲያ ያለፈች  ሁለተኛዋ ሀገር ትሆናለች፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች