ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች የሞሮኮ ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመለሱ

መስከረም 10፣2010

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር በሞሮኮ ሲስለጥኑ የነበሩ 19 ኢትየጵያዊያን አሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመለሱ።

በሞሮኮ ራባት ከተማ በተዘጋጀው ስልጠና በኢትየጵያ የተለያዩ የሊግ እርከኖች የሚገኙ ወንድ እና ሴት አሰልጣኞች የተካፈሉ ሲሆኑ በስልጠናው አዳዲስ የአሰለጣጠን መንገዶችን ቀስመዋል ተብሏል፡፡

ለሁለት ሳምንታት በቆየው ስልጠና የክፍል ውስጥ እና የመስክ ስልጠናዎች መውሰዳቸውን የገለጹት ሰልጣኞቹ በተለይ በወጣቶች እግርኳስ ላይ ምን አይነት ስልጠና መሰጠት እንዳለበት በርካታ አዳዲስ ትምህርቶችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናቸውን አጠናቀው ትናንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት ሰልጣኞቹ በቆይታቸው ከሞሮኮ የእግርኳስ አሰልጣኞች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸው ታውቋል።

ምንጭ ፡- ሶከር ኢትዮጵያ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች