ሊቨርፑር ከሊግ ካፕ ውጪ ሆነ

መስከረም 10፣2010

በእንግሊዝ የሊግ ካፕ ጨዋታ ወደ ኪንግ ፓወር ስታዲየም የተጓዘው ሊፐርፑል በሊሰተር ሲቲ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በመሸነፍ ከውድድሩ ውጪ ሆነ፡፡

የመጀመሪያውን አጋማሽ ያለ ግብ ያጠናቀቁት ክለቦችቹ ከእረፍት መልስ በ65ኛው ደቂቃ ኦካዛኪ የሊስተር ሲቲ የመጀመሪያ ጎል ሲያሰቆጥር እሱን ተክቶ ወደ ሜዳ የገባው አልጄሪያዊው አጥቂ ስሊማን ያስቆጠራት ግሩም ጎል ባለሜዳዎቹ ሊሰተሮችን  ወደ 4ተኛ ዙር አሸጋግራለች፡፡

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሊቨርፑል የበላይነት የነበረው ሲሆን በተለይም ብራዚላዊ ፊሊፕ ኮንቲኖ ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ አሳይቷል፡፡ በክረምት ቡድኑን የተቀላቀሉት አሌክስ ቻምበርሊን አና ዶሚኒክ ሶላክ ጥሩ የማግባት አጋጣሚዎችን ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰንን ያስፈረመው ክሪሰታል ፓላስ የመጀመሪያው ጨዋታው ሁደርፊልድ ታውንን አስተናግዶ በድል አጠናቋል፡፡ በሳኮ ብቸኛ ጎል ክሪስታልፓላሶች ወደ ቀጣዩ ዘሩ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ በሜዳው ዋይት ሃርትሌን በስሌን ያስተናገደው ቶተነሃም ሆትስፐር 65 ደቂቃዎች ያለግብ የተጨዋተ ሲሆን ዴሊ አሊ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል 4ተኛው ዙርን ተቀላቅለዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ አስቶን ቪላ 0-2 ሚድስብራ፤ዌስትሃም ዩናይትድ 3-0 ቦልተን ዎንደርስ፣ ሬዲንግ 0 -2 ስዋንሴ፤ብሬንትፎርድ1-3 ኖርዊች በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።

ጨዋታው ዛሬም ቀጥሎ ሲውል አርሰናል ከዶንካተ  ሮቨርስ፣ ቼልሲ ከኖቲንግ ሃም ፎረስት፣ ኤቨርተን ከሰንደርላንድ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከኮርተር አልቪዮንስ  ሲቲ ይጫወታሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች