በምሽት የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች አርሴናልና ኤሲሚላን ድል ሲቀናቸው ኤቨርተን ተሸንፏል

መስከረም 05፤2010

ትላንት ምሽት በተደረገው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች የእንግሊዙ አርሴናል የጀርመኑ ኮሎኝን አስተናግዶ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

20 ሺህ የሚጠጉ የኮሎኝ ደጋፊዎች ባስነሱት ሁከት ጨዋታው ለአንድ ሰዓት ዘግይቶ የጀመረ ሲሆን እንገግዳው ኮሎኝ በ9ኛው ደቂቃ በኮርዶባ አማካኝ ባስቆጠሩት ግብ የመጀመሪያው አጋማሽ በመሪነት አጠናቀዋል፡፡

ከእረፍት መልስ አርሴናል በኮላሲናች በ49ኛው ደቂቃ፤ ሳንቼዝ  በ67ኛው ደቂቃ እና በጨዋታ በመጠናቀቂ ላይ በሬሊን ባሰቆጠሩት ግቦች ጨዋታው 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት ባቴ ባሪሶቭእና ሬድ ስታር ቤልግሬድ  ጨዋታቸውን 1ለ1  አጠናቀዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ወደ ጣሊያን የተጓዘው ኤቨርተን በአትላንታ የ3ለ0 ያልተጠበቀ ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

ኤቨርተን በሳምንቱ መጨረሻ በፕሪምየር ሊጎ በቶነተነሃም 3ለ0 መሸነፉ ይታወሳል፡፡

በሌላ የምድቡ ጨዋታ ሊዮን ከአፖሎ ሊማሶል ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1  ተጠናቋል፡፡

ወደ ኦስትሪያ የተጓዘው ኤሲ ሚላን በበኩሉ 5 ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ በክረምቱ ዝውውር ከፖርቶ ያስመጡት አንድሬ ሲልቫ ሀትሪክ ሲሰራ ካልሃኖጎል እና ፈርናዴዝ ቀሪዎቹን የሚላን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች