ባን ኪሙን የአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስነ-ምግባር ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የነበሩት ባን ኪ ሙን የአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስነ-ምግባር ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ፡፡

ባን ኪሙን ከተመረጡ በኋላ በሰጡት መግለጫ የተሰጣቸው ሃላፊነት እጅግ ከባድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሊቀመንበርነት ቦታውን ከተረከቡ በኋላ የመጀመሪያ ስራቸው የሚሆነው የሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክን ጨምሮ ኦሎምፒክን ለማዘጋጀት በምርጫ ሂደቱ የተፈጠሩ የሙስና ድርጊቶችን ማጣራት ዋንኛ ጉዳያቸው እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ካሁን በኋላ በሚፈጠሩ የስነ ምግባር ጉዳዮች ላይ ጠበቅ ያለ ውሳኔ ማሳለፍ እንዳለበት ፕሬዝዳንቱ ቶማስ ባች አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ ዋሽንትገን ፖስት

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች