ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ከኬንያዊያኑ ከኪፕቾጌ እና ኪፕሳንግ ወሳኝ ፍልሚያ ይጠብቀዋል

ነሐሴ 25፣2009

መስከረም አጋማሽ በሚደረገው የበርሊን ማራቶን  የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊው ቀነኒሳ በቀለ ከኬንያዊያኑ ከኪፕቾጌ እና ኪፕሳንግ ጋር ወሳኝ ፍልሚያ ሊያደርግ ነው፡፡

ቀነኒሳ በቀለ እ.አ.አ በ2016 በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በጉዳት በ6 ሰከንድ ዘግይቶ ክብረ ወሰኑን ማጣቱ ይታወሳል፡፡

የኦሎምፒክ ማራቶን አሸናፊው እና በርቅቱ በዓለም ሶስተኛ ምርጥ ሰዓት ያለው ኪፕቾጌ አዲስ ክብረ ወሰን ለመስበር ዕድል ያለው አትሌት መሆኑን የበርሊን ማራቶን አዘጋችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በኪሚቶ ክብረ ወሰኑን የተነጠቀው ሌላው ኬኒያዊ ኪፕሳንግ ደግሞ  በውድድሩ ሌላው ተጠባቂ አትሌት ነው፡፡

በዚህ ውድድር ሶስቱም አትሌቶች በሚያደርጉት ፉክክር አዲስ ክብረ ወሰን ሊሰበር እንደሚችል ተጠብቋል፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በ5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር የክብረ ወሰን ባለቤት መሆኑ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡‑ ሮይተርስ

 

 

 

 

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች