ግሸምን ፋርማሲ የተከለከለ መድሃኒት በመሸጡ እግዳ ተጣለበት

ነሐሴ 23፣2009

የግሸን ፋርማሲ በስፖርት የተከለከለ መድኃኒት ህጋዊ ባልሆነ መልኩ እንደሚሸጥ በመረጋገጡ የ6 ወራት እገዳ እንደተጣለበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለውን EPO ወይም በሳይንሳዊ ስያሜው Erythropoietin የተባለውን መድኃኒት በተለምዶ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የግሸን ፋርማሲ ያለምንም የሐኪም ትዕዛዝ እንደሚሸጥ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም መረጃውን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት እና በፌዴራል እና በአዲስ አበባ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣናት በተደረገ ምርመራ መድሃኒቱ  በግሸን ፋርማሲ እንደሚገኝ ተረጋጧል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ስታዲዮም አካባቢ የሚገኘው  የግሸን ፋርማሲ ለሶስት ተከታታይ ወራት እንዲዘጋና አገልግሎት እንዳይሰጥ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

በተጨማሪም የቅርንጫፍ መድኃኒት ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ይበልጣል አድማሱ የሙያ ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ በመሆኑ፣ የሙያ ፈቃዳቸው ለስድስት ወራት እንዲታገድና ፈቃዳቸውንም ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲመልሱ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች