ትላንት ሲጠበቅ በነበረው የዙሪኩ ዳያመንድ ሊግ ሙክታር እድሪስ በ2ተኛነት አጠናቀቀ

ነሐሴ 19፣2009

ትላንት ሲጠበቅ በነበረው የዙሪኩ ዳያመንድ ሊግ የ5ሺህ  ሜትር ሩጫ የለንደኑ የአለም ሻምፒዮን  ሙክታር እድሪስ ሞፋራህን ተከትሎ በ2ተኛነት አጠናቋል፡፡

በትላንትናው ዕለት ስዊስዘርላንድ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያኖቹ ሙክታር እድሪስና ዮሚፍ ቀጀልቻ ከሞ ፋራህ ጋር እስከ መጨረሻ ሰዓቷ ድረስ በትንቅንቅ  ነው የጨረሱት፡፡ሙክታር በሩጫው ማጠናቀቂያ መስመር አቅራቢያ ተረግጦ በመውደቁ ሞ ፋራህን ተከትሎ ገብቶ የነበረው አሜሪካዊ ፓውል ቺሊሞ ጥፋት ሰርቷል በሚል ውጤቱ ተሰርዞ ለሙክታር ተሰጥቷል፡፡በለንደኑ ሻምፒዮን ትልቅ የቡድን ስራ በመስራት ምስጋና ያተረፈው ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ በትላንትናው ሩጫ በሶስተኛነት አጠናቋል፡፡ ሰለሞን ባረጋ ደግሞ በአራተኛነት ጨርሷል፡፡የኔው አለምረውና ብርሃኑ ለገሰም የውድድሩ ተካፋዮች ነበሩ፡፡

ሞፋራ ራሱን ከመም ሩጫ በሚያገልበት በዚህ መድረክ አሸናፊ ሆኖ በመውጣቱ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡

በሌሎች የዙሪኩ መድረክ ከተሳፉት ኢትዮጵያዊያን መካከል ሀብታም አለሙ በሴቶች የ800 ሜትር በአገር ደረጃ ክብረ ወሰን በሆነ ሰዓት የደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰመኒያ በሻነፈችበት መድረክ 4ተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

በ3ሺህ መትር መሰናክል ሶፊያ አሰፋና እቴነሽ ድሮ ቢወዳደረውም ድል አልቀናቸውም፡፡

ምንጭ፡‑ ዳያመንድ ሊግ

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች