ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአምስት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት

ነሃሴ 8፤2009

ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ለስፔን ሱፐር ካፕ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አድረገው ማድሪድ 3ለ1 ሲረታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ በመውጣቱና ዳኛውን በመገፋቱ የአምስት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት፡፡

ሮናልዶ ማድሪድ 2ለ1 መምራት የቻለበትን ግብ ካስቆጠረ በኋላ ማሊያውን በማውለቁ የመጀመሪያውን ቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ ያየ ሲሆን ሁለተኛውን ደግሞ ፍጹም ቅጣት ለማግኘት ስትል አስመስለህ ወድቀሃል በሚል ነበር ያየው፡፡

ከዚህ በኋላ ስሜታዊ የሆነው ሮናልዶ ዳኛውን በመጋፋቱ በሀገሪቱ እግር ኳስ ፈደሬሽን በአጠቃላይ የአምስት ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

ሮናልዶ እስከ መጪው መስከረም ድረስ በላሊጋው የማይጫወት ሲሆን በሻምፕዮንስ ሊጉ ግን መጫወት እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች