በ5 ሺህ ማጣሪያ አልማዝ፣ ሰንበሬ እና ለተሰንበት ወደ ፍጻሜው ውድድር አልፈዋል

ነሐሴ 05፣2009

በ16ኛው የለንደን አትሌትክስ ሻምፕዮና ትናንት ምሽት በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይ፣ አልማዝ አያና እና ሰንበቴ ተፈሪ ወደ ፍጻሜው ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በሁለተኛው ምድብ በተካሄደ የማጣሪያ ውድድር ለተሰንበት ግደይ ከምድቡ አንደኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜው ውድድር ማለፏን አረጋግጣለች፡፡

 በምደብ አንድ በተካሄደው ማጠሪያ ውድድርም አልማዝ አያና እና ሰንበሬ ተፈሪ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አልፈዋል፡፡

በውድድሩ ኬንያዊቷ ሄለን ኦንሳዶ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡

የሴቶች 5 ሺህ ፍጻሜ ውድድር እሁድ ነሐሴ 7/2009 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች