ኢትዮጵያ በሁለት የፍፃሜ ውድድሮች ዛሬ ትሳተፋለች

ነሃሴ 02፤ 2009

ዛሬ ምሽት በሚደረጉ የወንዶች 800 ሜትርና 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ወድድሮች ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ፡፡

መሃመድ አማን በ800 ሜትር ፍፃሜ ምሽት 5፡35 ውድድሩን ያደረጋል፡፡

መሃመድ አማን  በማጣሪያው ምርጥ ሰዓት ካላቸው አትሌቶች መካከል ሁለተኛ ነው፡፡

መሃመድን በምሽቱ ከሚፎካከሩት 9 አትሌቶች መካከል በአስመዘገበው የዓመቱ ምርጥ ሰዓት መሰረት 8ኛ ነው፡፡

በርቀቱ የቦትስዋናው ኒጀል አሞስ እና ኬኒያዊው ኪፕዮጌን ፒቲ በዓመቱ የተሻለ ሰዓት አስመዝግበዋል፡፡

ምሽት 5:10 ሰዓት ደግሞ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ጌትነት ዋሌ፣ ታፈሰ ሰቦቃና ተስፋዬ ድሪባ በኢትዮጵያ በኩል ይሰለፋሉ፡፡

ጌትነት ዋሌ በ8፡12 ደቂቃ ከኢትዮጵያውያኑ የተሻለ ሰዓት ያለው አትሌት ነው፡፡

በዓመቱ አሜሪካዊው ጃጋር 8፡01.29 ሰዓት በመያዝ ቀዳሚው አትሌት ነው፡፡ ኬኒያውያኖቹ ብሪች እና ኪፕሪቶ በበኩላቸው በዓመቱ ምርጥ ሰዓት ያላቸው አትሌቶች ናቸው፡፡

የሞሮኮው አትሌት ሶፊያንም በዓመቱ ውድድሩን 8፡5 ደቂቃ በማስመዝገቡ ግምት የተሰጠው አትሌት ነው፡፡ 

በመሆኑም በ3ሺህ ሜትር መሰናክል ከ5 በላይ አትሌቶች ከኢትዮጵያውያን የሚልቅ ሰዓት ይዘው ውድድሩን ያደርጋሉ፡፡

ምንጭ፡ አለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽን

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች