የኔይማር የክብረ ወሰን ዝውውር በቁጥሮች ሲቀመጥ

ሐምሌ 28 ፤2009

የብራዚሉ የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ከባርሲሎና ወደ ፈረንሳዩ ፓርሴንት ጀርመን የተዘዋወረበት 200 ሚሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዝብ እግር ኳሱ ታሪክ አዲስ ክበረ ወሰን ሆኗል፡፡

ኔማር በፓርሴንት ጀርመን 5 ዓመት ለመቆየት ሲስማማ በዓመት 26.8 ሚሊዮን ፓውንድ ከታክስ ውጭ ያገኛል፡፡

በአጠቃላይ 5 ዓመት ደግሞ 450 ሚሊዮን ፓውንድ ገንዘብ ወደ ካዝናው ያስገባል፡፡

ይህም የዓመቱ ደሞዝ ሲሸነሸን 515 ሺህ ፓውንድ በሳምንት፣ 73 ሺህ 571 ፓውንድ በቀን ፣ 3ሺህ 65 ፓውንድ በየሰዓቱ እና 57 ፓውንድ በየደቂቃው እንደሚያገኝ  ያስረዳል፡፡

ኔይማር ይህን ገንዘብ ወደ ገበያ ይዞ ቢወጣ ደግሞ በ22 ወር ደሞዙ የቅንጦት የግሉን አውሮፕላን መግዛት ያስችለዋል፡፡

የ27 ሰዓት ደሞዙ ደግሞ የቅንጦት መኪና ለመግዛት ያስችለዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ ድንበር ለመገንባት ለያዙት ዕቅድ 95 ኔማሮች ያስፈልጉታልም ተብሎ ለንፅፅር ቀርቧል፡፡

ምንጭ፡ ስካይ ስፖርት፣ቢቢሲ … 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች