አንቶኒዮ ኮንቴ የሁለት አመት ኮንትራት ከቼልሲ ጋር ተፈራረመ

ሃምሌ 12፤2009

የቼልሲው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በስታብፎርድ ብሪጅ የሚያቆየውን ተጨማሪ ሁለት አመታትን  ስምምነት ፈረመ፡፡

በ2016 ምዕራብ ለንደን ቼልሲን የተቀላቀለው ኮንቴ እስከ 2019 የሚያቆየውን የሶስት ዓመት ስምምነት ፈርሟል፡፡

አዲስ ስምምነት መፈረሜ በጣም አስደስቶኛል ያለው የ47 ዓመቱ አንቶኒዮ ኮንቴ በባፈው የውድድድር ዘመን ጠንክር በመስራታችን የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መሆን ችለናል አሁንም ከዚህ የበለጠ በመስራት አሸናፊ እንሆናል በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በአዲሱ ስምምነት መሰረት በአመት 9 ሚሊዮን ፓውንድ አመታዊ ክፍያን ያስገኝለታል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች