ቅዱስ ጊዮርጊስ በቻምፒየንስ ሊጉ 3ተኛውን ሽንፈት አስተናገደ

ሀምሌ 3፣2009

በቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ትላንት ከቱኒዝያውን ኤስፔራንስ ዱቱኔዝ ጋር ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-0 በሆነ ውጤት ተሸነፈ፡፡

ከምድቡ አለማለፉን አውቆ ወደ ቱኒዝያ ያቀናው ቅዱስ ጊዩርጊስ በምድቡ ሶስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

በዚው ምድብ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የኮንጎ ቪታን አስተናግዶ 1-1 ተለያይተዋል፡፡

ቅዱስ ጊዩርጊስ በሚገኝበት ምድብ 3 ኤስፔራንስ በ12 ነጥብ አንደኛ ሲሆን ማሚሎ ሰንዳውን በ9 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችለዋል፡፡

በምድብ አንድ ኤቶዋልደ ሳህል እና ፊሮቬራ ቤራ፣ ከምድብ ሁለት ዩኤስ ኤም አልጄርስ እና አል አህሊ ትሪፖሊ ፣ ምድብ ሶስት ኤስፔራንስ እና ማሚሎ ሰንዳውን ከምብድ አራት ዋይዳ ካሳብላንካ እና አል አሊ ወደ ሩብ ፍጻሜው መቀላቀል ችለዋል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች